The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesAlms Giving [Al-Maun] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah Alms Giving [Al-Maun] Ayah 7 Location Maccah Number 107
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በምርመራው ቀን የሚያስተባብለውን ሰው አየህን? (አወከውን?)
ይሀውም ያ የቲምን በኃይል የሚገፈትረው፤
ድሃን በማብላት ላይም የማያነሳሳው ነው።
ወዮላቸው ለሰጋጆች፤
ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት (ሰጋጆች)፤
ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለሆኑት፤
የዕቃ ትውስትንም ሰዎችን የሚከለክሉ ለሆኑት ሁሉ ወዮላቸው::

